ባሕር ዳር: የካቲት 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ፋሲል ከነማ የ16ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታውን ከሀድያ ሆሳዕና ጋር ቀን 9:00 በአዲስ አበባ ስታዲየም ያደርጋል።
አጼዎቹ እስካሁን 18 ጨዋታዎችን አድርገዋል።በስምንቱ በማሸነፍ፣ በዘጠኙ አቻ በመለያየት፣ በአንዱ በመሸነፍ በሰባት የንጹህ የግብ ክፍያ እና 33 ነጥብ በመያዝ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ከመሪው ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት ሁለት ብቻ ነው።
ቡድኑ ጠንካራውን የተከላካይ ክፍል ይበልጥ አጠናክሮ እና የሚስተዋልበትን የማጥቃት ውስንነት ቀርፎ ዛሬ ካሸነፈ ነጥቡን 36 በማድረስ የሊጉ መሪ ይኾናል።
ተጋጣሚው ሀድያ ሆሳዕና ከ18 ጨዋታዎች 21 ነጥብ በመያዝ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ሊጉን ሲዳማ ቡና፣ ሃዋሳ ከተማ እና ነገሌ አርሲ በቅደም ተከተል ይመሩታል። ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ ወላይታ ድቻ እና አርባ ምንጭ ከተማ ወራጅ ቀጣና ውስጥ ይገኛሉ።
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



