የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ፌስቲቫል በእግር ኳስ የፍጻሜ ተፋላሚዎች ተለዩ።

0
4

 

አዲስ አበባ: ጥር 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በጅማ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ፌስቲቫል የቀጠለ ሲኾን ዛሬ ረፋድ በእግር ኳስ የግማሽ ፍጻሜ ውድድሮች ተካሂደዋል።

በወንዶች ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ እና የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ፤ በሴቶች ደግሞ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ እና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለፍጻሜ ደርሰዋል ።

በወንዶች እግር ኳስ ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ መቱ ዩኒቨርሲቲን 1ለ0፣ ኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ዲላ ዩኒቨርሲቲን በመለያ ምት 9ለ8 በማሸነፍ ነው ለፍጻሜ የደረሱት።
ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ባሳለፍነው ዓመትም በወንዶች እግር ኳስ የፍጻሜ ተፈላሚ እንደነበር ይታወሳል ።

በወንዶች ፍጻሜ ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

በተመሳሳይ በሴቶች እግር ኳስ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን፣ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አምቦ ዩኒቨርሲቲን 3ለ1 በማሸነፍ ለፍጻሜ ደርሰዋል።

በሴቶች ፍጻሜም ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይገናኛሉ።

የእግር ኳስ የፍጻሜ ጨዋታዎች የፊታችን እሁድ የሚካሄዱ ይኾናል።

ከ49 ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ከ7 ሺህ 500 በላይ ልዑካን የተሳተፉበት እና ተወዳዳሪዎች በ15 የስፖርት አይነቶች ፉክክር ያደረጉበት 10 የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ፌስቲቫል የፊታችን እሁድ የካቲት 1/2018 ዓ.ም ፍጻሜውን ያገኛል።

ዘጋቢ:- ባዘዘው መኮነን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here