ሞሮኮ ‘ይግባኝ’ አለች።

0
21
ባሕር ዳር: ጥር 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሞሮኮ እና ሴኔጋል ለፍጻሜ መገናኘታቸው ይታወሳል።
በጨዋታው ሴኔጋል “ያስቆጠርሁት ግብ ያላግባብ ተሽሮብኛል” በሚል ከዳኛው ጋር እሰጥ አገባ መግባቷ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።
የዕለቱ ዳኛም የሴኔጋል ተጫዋች በሞሮኮ ተጫዋች ላይ “ፈጸሙት” ላሉት ጥፋት በቫር ድጋፍ ፍጹም ቅጣት ምት ሰጥተዋል። በዚህ ምክንያት በተፈጠረ አለመግባባት ጨዋታው ለ17 ደቂቃ ተቋርጦ ነበር።
በወቅቱ የተፈጸመውን የስፖርታዊ ሥነ ምግባር መጓደል ፊፋም ኾነ ካፍ በጽኑ አውግዘውታል። ካፍም ጉዳዩን በዋናነት በተንቀሳቃሽ ምሥል እና በፎቶ ግራፍ አስደግፎ በመመርመር ጥፋተኛ ናቸው ባላቸው የሁለቱን ሀገራት የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች በገንዘብ፣ ጥፋተኛ በተባሉት ተጫዋቾች እና የሴኔጋልን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ በጨዋታ እግድ መቅጣቱ ይታዎሳል።
ሞሮኮ ታዲያ ከሰሞኑ ቅጣቱን በተመለከተ ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ‘ይግባኝ’ ብላለች።
ፊልሞጋት ዶት ኮም እንዳስነበበው ቅጣቱ ከልክ ያለፈ እና ኢ ፍትሐዊ ነው ያለችው ሞሮኮ ጉዳዩን ካፍ እንደገና እንዲመረምረው እና ውሳኔውን እንዲያስተካክል ነው የጠየቀችው።
ካፍ ጉዳዩን በአንክሮ መርምሮ ማስተካካያ የማያደርግ ከኾነም ይግባኙን ለፊፋ እንደምታቀርብ ነው ሞሮኮ ያስታወቀችው።
በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሴኔጋል ሞሮኮን 1ለ0 አሸንፋ የዋንጫ አሸናፊ መኾኗ ይታዎሳል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here