በስፔን፣ በጣሊያን እና በፈረንሳይ የሚደረጉ የዛሬ ጨዋታዎች

0
18
ባሕር ዳር: ጥር 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በስፔን ኮፓ ዴላሬይ ዛሬ በሩብ ፍጻሜ ሪያል ቢትስ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ይጫወታሉ። ጨዋታው ምሽት 5:00 ላይ ይካሄዳል።
ሁለቱ ቡድኖች በሁለት የኮፓ ዴላሬይ ጨዋታዎች ተገናኝተው አትሌቲኮ ማድሪድ በአንድ ጨዋታ ሲያሸንፍ በአንዱ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።
በጣልያን ኮፓ ኢታሊያ በሩብ ፍጻሜ ዛሬ አታላንታ ከጁቬንቱስ ምሽት 5:00 ላይ ይጫወታሉ። ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ ቀደም በስምንት የኮፓ ኢታሊያ
ጨዋታዎች ተገናኝተዋል። ጁቬንቱስ በአምስት ጨዋታዎች በማሸነፍ የበላይነቱን ይዟል። አታላንታ በሁለት ጨዋታዎች ድል አድርጓል። በአንድ ጨዋታ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።
በሌላ ጨዋታ በፈረንሳይ ኮፓ ዴ ፍራንስ ስትራስበርግ ከሞናኮ ምሽት 5:00 ላይ ይጫወታሉ።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here