ባሕር ዳር፡ ጥር 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በጣሊያን ዋንጫ ኢንተር ሚላን ቶሪኖን አሸንፎ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ተቀላቅሏል።
ኢንተር ሚላን ቶሪኖን 2ለ1 በማሸነፍ ነው ለግማሽ ፍፃሜው ማለፉን ያረጋገጠው።
በስፔን የንጉሱ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታም ሪያል ሶሲዳድ አላቪስን 3ለ2 እና አትሌቲክ ቫሌንሲያን 2ለ1 በማሸነፍ የግማሽ ፍጻሜ ተፋላሚነታቸውን አረጋግጠዋል።
በተመሳሳይ በጀርመን ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ስቱትጋርት ሆልስታይን ኪልን 3ለ0 አሸንፏል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



