ኒጎሎ ካንቴ ከሳውዲ ወደ ቱርክ አቅንቷል።

0
11
ባሕር ዳር: ጥር 27/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የቱርኩ ክለብ ፌነርባቼ ፈረንሳዊውን አማካኝ ኒጎሎ ካንቴን ከሳውዲ ፕሮ ሊግ ክለብ አል ኢቲሃድ ማስፈረሙን አረጋግጧል።
የፈረንሳዊው ተጨዋች ወደ ቱርክ የማምራት ተስፋ ማክሰኞ ዕለት ተሟጦ የነበረ ይመስል ነበር። በወቅቱ ፌነርባቼ ባወጣው መግለጫ ለዝውውሩ መፍረስ አል ኢቲሃድን ተጠያቂ አድርጎ ነበር።
ፌነርባቼ እንደገለጸው ከኾነ አል ኢቲሃድ የሞሮኮውን አጥቂ ዮሱፍ ኤን ነሲሪን ወደ ወደ አል ኢቲሃድ የሚያዘዋውረውን ሰነድ በወቅቱ አላጠናቀቀም ነበር።
ኾኖም ግን በዛሬው ዕለት ፌነርባቼ ችግሩ መፈታቱን እና የቀድሞው የቼልሲ ተጨዋች ካንቴ በሳውዲ አረቢያ ለሁለት ዓመት ተኩል ከቆዬ በኋላ ክለቡን መቀላቀሉን አረጋግጧል።
የ34 ዓመቱ ካንቴ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2023 ከቼልሲ ወደ አል ኢቲሃድ መዘዋወሩ ይታወሳል። ከለንደኑ ክለብ ጋር ሻምፒዮንስ ሊግ፣ ፕሪሚየር ሊግ፣ ዩሮፓ ሊግ እና የኤፍኤ ካፕ ዋንጫዎችን አንስቷል።
ካንቴ ሰማያዊዎቹን ከመቀላቀሉ በፊት በ2016 ሌስተር ሲቲን ለታሪካዊ የፕሪሚየር ሊግ ድል ማብቃቱ ይታወሳል።
የ28 ዓመቱ ኤን ነሲሪ ደግሞ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ክለቡን ለቆ ወደ ተቀናቃኙ አል ሂላል የተዘዋወረውን የቀድሞ የሪያል ማድሪድ አጥቂ ካሪም ቤንዜማን በመተካት አል ኢቲሃድን ተቀላቅሏል።
በቴዎድሮስ ኃይለኢየሱስ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here