ባሕርዳር: የካቲት 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) አሠልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ ነው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ሆኖ የተሾመው፡፡
ቡድኑ በጋና አስተናጋጅነት በሚካሄው የአፍሪካ ጨዋታዎች ውድድር ላይ ተሳታፊ መሆኑ ይታወሳል።
ከየካቲት 29 ቀን ጀምሮ ለሚካሄው ውድድርም ቡድኑን እንዲያዘጋጅ አሠልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ መሾሙን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ገልጿል፡፡
አሠልጣኝ ዮሴፍ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሚሳተፈውን የአርባምንጭ ከተማ የሴቶች ቡድንን በማሠልጠን ላይ ነበር፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!