ባሕር ዳር፡ ጥር 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ሊግ ካፕ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ አርሰናል እና ቼልሲ ያደረጉት ጨዋታ በአርሰናል አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
አርሰናል ቸልሲል 1ለ0 ማሸነፍ ችሏል።
የአርሰናልን የማሸነፊያ ግብ ሀቨርትዝ አስቆጥሯል።
አርሰናል ከሁለት ሳምንት በፊትም በስታምፎርድ ብሪጅ የነበረውን የመጀመርያ ዙር ጨዋታ 3ለ2 ማሸነፉ የሚታወስ ሲኾን በአጠቃላይ ውጤት 4ለ2 በኾነ ውጤት ለፍጻሜው ጨዋታ መድረሱን አረጋግጧል።
የሊግ ካፕ የፍጻሜ ጨዋታው በግዙፉ የዌይምብሌ ስታዲየም የሚደረግ ይኾናል። አርሰናልም ለዚህ ፍጻሜ ጨዋታ ከማንቸስተር ሲቲ እና ኒውካስትል ዩናይትድ አሸናፊ ጋር የሚጫዎት ይኾናል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!መ



