የፕሪምየር ሊጉ የጥር ተጫዋቾች ዝውውር ተዘግቷል።

0
23

 

የጥር ወር የተጫዋቾች ዝውውር ለእንግሊዝ ቡድኖች በይፋ መዘጋቱን ቢቢሲ ዘግቧል። የተለያዩ ቡድኖችም ያስፈረሟቸውን እያሳወቁ ነው። መዚህም መሠረት፦

👉 ሼፍ ዩናይትድ የማንቸስተር ሲቲውን አማካይ ካልቪን ፊሊፕስን በውሰት ውል አስፈርሟል።

👉 ክሪስታል ፓላስ ስትራንድ ላርሰንን በ48 ሚሊዮን ፓውንድ ከወልቭስ ማስፈረሙን አሳውቋል።

👉 ሴልቲክ ኦስትሪያዊውን አጥቂ ጁኒየር አዳሙን ከጀርመኑ ፍሬይበርግ ቡድን ላይ በውሰት ውል አስፈርሟል።
የ24 ዓመቱ ተጫዋቹ የተወለደው ናይጄሪያ ውስጥ ነው።

👉 ቶትንሃም የ18 ዓመቱን የሃርትስ አጥቂ ጀምስ ዊልሰንን በውሰት ውል አስፈርሟል።

‎👉 ፊዮሬንቲና ዳኒኤል ሩጋኒን ከጁቬንቱስ ላይ በዉሰት ውል ማስፈረሙን ኢታሊያን ኢን ፔፐር አስነብቧል።

👉 ሰንደርላንድ ከኢኳዶራዊው የአንደርሌክት ተጫዋች ኒልሰን አንጉሎን ጋር በ17 ነጥብ 5 ሚሊዮን ፓውንድ ውል አስፈርሟል።

👉 አትሌቲኮ ማድሪድ የ28 ዓመቱ ናይጄሪያዊ አድሞላ ሉክማንን ለማስፈረም በመርሕ ደረጃ ተስምቷል።

👉 ጁቬንቱስ ኤሚል ኾልምን ከቦሎኛ በውሰት ዉል ማግኘቱ ተረጋግጧል።

በሙሉጌታ ሙጨ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here