የ24ኛ ሳምንት ቀሪ ጨዋታ ዛሬ ይደረጋል።

0
29
ባሕር ዳር: ጥር 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ​የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ24 ሳምንት የመጨረሻ መርሐ ግብር ዛሬ ሰንደርላንድ ከበርንሌይ በስታዲየም ኦፍ ላይት ምሽት 5:00 በሚያደርጉት ጨዋታ ይቋጫል።
ሰንደር ላንድ በፕሪምየር ሊጉ ከደረጋቸው 23 ጨዋታዎች በስምንቱ አሸንፎ፣ በዘጠኙ አቻ ተለያይቶ፣ በስድስቱ ተሸንፎ እና 33 ነጥብ በመያዝ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ለቡድኑ የዛሬው ጨዋታ ወሳኝነቱ ከፍተኛ ነው። ምክንያቱ ደግሞ ጨዋታውን ካሸነፈ ደረጃውን ወደ ሰባተኛነት ከፍ ማድረግ ስለሚያስችለው ነው። በመኾኑም ጠንካራ ፉክክር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ተጋጣሚው በርንሌይ ከ23 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በሦሥት ጨዋታዎች ብቻ ነው። በስድስቱ አቻ ተለያይቶ በ14 ተሸንፎ 15 ነጥብ ብቻ በመያዝ ወራጅ ቀጣናው ውስጥ 19ኛ ላይ ይገኛል።
ቡድኑ ሰንደርላንድን ቢያሸንፍ ከወራጅ ቀጣናው የሚያስወጣው ባይኾንም ነጥቡን ከፍ ማድረግ ግን ያስችለዋል።
ሁለቱ ቡድኖች በተገናኙባቸው ሰባት የቅርብ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች በርንሌይ በሦሥቱ በማሸነፍ የበላይነትን ይዟል። ሰንደርላንድ ደግሞ በሁለቱ አሸንፏል። በሁለቱ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።
በዛሬው ጨዋታ ሰንደርላንድ ደረጃውን ከፍ ለማድረግ በርንሌይ ደግሞ ከወራጅ ቀጣናው ነጥብ ሠብሥቦ ለመውጣት ስለሚረዳው ጨዋታው ለሁለቱም ወሳኝነት አለው።
ሊጉን አርሰናል በ53 ነጥብ እየመራው ይገኛል።ማንቸስተር ሲቲ በ47 ነጥብ ይከተላል። አስቶን ቪላ በ46 ነጥብ ሦሥተኛ ደረጃን ይዟል።
ዌስትሃም፣ በርንሌይ እና ዎልቭስ ወራጅ ቀጣናው ውስጥ ይገኛሉ።
ዘጋቢ፦ሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here