አጫጭር የዝውውር ወሬዎች:-

0
48
ባሕር ዳር: ጥር 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የ2025/2026 የጥር ወር የተጫዋቾች ዝውውር ነገ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። የተለያዩ ቡድኖችም ተጫዋቾችን እያዛወሩ ይገኛሉ።
👉 የክሪስታል ፓላሱ ዣን ፊሊፕ ማቴታ ኤሲ ሚላንን ለመቀላቀል ተስማምቷል።
ተጫዋቹ ከኤሲ ሚላን ጋር እስከ 2030 የሚያቆየውን ውልም በሰዓታት ውስጥ ይፈርማል ነው የተባለው።
👉 አሠልጣኝ ማይክል ካሪክ በማንቸስተር ዩናይትድ የሚቀጥል ከኾነ ማርከስ ራሽፎርድን የመመለስ ፍላጎት አለው ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
👉 ፉልሃም ለጆ ዊሎክ ያቀረበውን 20 ሚሊየን ፓውንድ የዝውውር ገንዘብ ኒውካስትል ዩናይትድ ውድቅ ማድረጉን አስታውቋል በማለት ያስነበበው ዴይሊ ሜይል ነው።
👉 ሰንደርላንድ የ25 ዓመቱን ፈረንሳዊ የፊት መስመር ተጫዋች ዊልሰን ኢሲዶርን ለናፖሊ ቡድን ለመሸጥ መስማማቱን የዘገበው ካልሲዮመርካቶ ነው።
👉 ሊቨርፑል እና ቼልሲ የ20 ዓመቱን ፈረንሳዊ ተከላካይ ጄረሚ ዣኬትን ለማስፈረም ከሬኔስ ቡድን ጋር እየተነጋገሩ መኾናቸውን ፋብሪዚዮ አስነብቧል።
👉 ቼልሲ ለስትራስቦርግ ቡድን በውሰት ሰጥቶት የነበረውን የ20 ዓመቱን ሴኔጋላዊ ተከላካይ ማማዱ ሳርን መልሶ በመውሰድ ሊያጫውተው መኾኑን ስካይ ስፖርት ዘግቧል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here