ዱባይ በተካሄደ ማራቶን ኢትዮጵያውያን ድል አደረጉ።

0
146
ባሕር ዳር፡ ጥር 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የዱባይ 2026 የማራቶን ውድድር ዛሬ ሲካሄድ ኢትዮጵያውያን በሁለቱም ጾታ የበላይነቱን በመያዝ አሸንፈዋል።
በሴቶች በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያውያኑ እስከ 10 ያለውን ደረጃ በመያዝ ነው በበላይነት ያጠናቀቁት። በዚህ ውድድር አንችናሉ ደሴ በአንደኝነት ስትፈጽም ሙሉየ ደከቦ ሁለተኛ እና ፋንቱ ወርቁ በሦሥተኛ ደረጃ አጠናቅቀዋል።
በወንዶቹ በተካሄደ የማራቶን ውድድር ደግሞ ሩዋንዳዊው አትሌት ሦሥተኛ ከመውጣቱ ውጭ እስከ 10 ያለውን ደረጃ ኢትዮጵያውያኑ ተቆጣጥረዋል።
በዚህ ውድድር ንብረት መላክ በአንደኛነት ሲጨርስ ያሲን ሀጅ ደግሞ ሁለተኛ ኾኗል። ሩዋንዳዊው አትሌት ጆን ሀኪዚማን ሦሥተኛ ኾኖ ጨርሷል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here