ካፍ ሴኔጋልን እና ሞሮኮን ቀጣ

0
32
ባሕር ዳር: ጥር 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሞሮኮ ባዘጋጀችው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሞሮኮን ከሴኔጋል ለፍጻሜ ማገናኘቱ ይታዎሳል።
በጨዋታ ላይም የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ተከስቶ ጨዋታው ለ17 ደቂቃ ያህል መቋረጡ አይዘነጋም።
ክስተቱም በካፍ እና ፊፋ በከፍተኛ ኹኔታ ተወግዟል። ይህን ተከትሎም ካፍ የሴኔጋል እና ሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን አባላት እና ፌዴሬሽኖችን መቅጣቱን አሳውቋል።
የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ፓፔ ቲያው ጨዋታው እንዲቋረጥ ባደረጉት የስፖርታዊ ጨዋነት መጎደል ባሕርይ የአምስት ካፍ ጨዋታ እግድ እና የ100 ሺህ ዶላር ቅጣት ተጥሎባቸዋል።
ኢሊማን ሼክ ባሮይ ንዲያዬ የተባለው ተጫዋች በዳኛው ላይ ባሳየው ያልተገባ ባሕርይም በሁለት የካፍ ጨዋታዎች እንዳይሳተፍ ተቀጥቷል።
ኢስማኢላ ሳርም ሌላው ተጫዋች በሁለት የካፍ ጨዋታዎች እግድ ተላልፎበታል።
የሴኔጋል እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ደጋፊዎች፣ ተጫዋቾች እና የቴክኒክ ቡድን አባላት ባሳዩት ያልተገባ ባሕርይ በድምሩ ከ600 ሺህ በላይ ዶላር ተቀጥቷል።
ሞሮኮ የቡድኑ ተከላካይ አሽራፍ ሐኪሚ ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጭ በኾነ ባሕሪው ሁለት የካፍ ጨዋታዎችን ታግዷል።
አማካዩ ኢስማኤል ሳይባሪ የሦሥት ጨዋታዎች እገዳ እና የ100 ሺህ ዶላር ቅጣት ተቀጥቷል።
የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጨዋታው ወቅት ኳስ አቀባዮች ለፈጸሙት ተገቢ ያልኾነ ባሕርይ 200 ሺህ ዶላር እንዲከፍል ተወስኗበታል፡፡
በቫር የመመልከቻ አካባቢ የተለያዩ ቁሳቁሶችን በመወርወር እና ዳኛውን በማደናቀፍ ፌዴሬሽኑ ተጨማሪ 100 ሺህ ዶላር እንዲከፍልም ተወስኖበታል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here