በክብረ ወሰኖች የታጀበው የታሪክ ምዕራፍ።

0
23
ባሕር ዳር: ጥር 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሞሮኮ አስተናጋጅነት የተካሄደው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ፣ በሜዳ ላይ ፉክክር ብቻ ሳይኾን በገቢ፣ በተደራሽነት እና በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ረገድ አዳዲስ ታሪኮችን በመጻፍ ተጠናቅቋል።
ውድድሩ ሴኔጋልን የዋንጫ፣ ሞሮኮን ሁለተኛ እንዲሁም ናይጀሪያ ሦሥተኛ አድርጎ መጠናቀቁ ይታወሳል።
ካፍ ኒውስ እንደዘገበው ይህ የውድድር ዘመን ቀደምት ክብረ ወሰኖችን የሰባበሩ ትዕይንቶችን አስመዝግቦ ነው በስኬት የተጠናቀቀው
ከተመዘገቡ አዳዲስ ክስተቶች መካከል፦
👉111 ታዋቂ እና ስመ ጥር ዓለም አቀፍ የመገናኛ ተቋማት ውድድሩን በቀጥታ ማስተላለፋቸው ክስተቱን ልዩ አድርጎታል።
👉በዓለም ዙሪያ ለ6 ነጥብ1 ቢሊዮን ሕዝብ ተደራሽ በመኾንም የአፍሪካ እግር ኳስ ያለውን ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ማረጋገጥ ችሏል።
👉ለመጀመሪያ ጊዜ በቲክ ቶክ መድረክ ለ1 ሚሊዮን ሰዎች በቀጥታ በምስል ተደራሽ መኾኑ ሌላው ክስተት ነው።
👉23 ታላላቅ ተቋማት ውድድሩን በስፖንሰርሺፕ መደገፋቸው ሌላው ጉዳይ ነው።
👉ከስፖንሰርሺፕ ብቻም ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ በላይ ገቢ ተገኝቷል። ይህም ካለፉት ውድድሮች ጋር ሲነጻጸር የ90 በመቶ ብልጫ አለው።
ካፍ እንደገለጸው በዚህኛው ውድድር የተገኘው ገቢ እስካሁን ከተደረጉት ሁሉም የአፍሪካ ዋንጫዎች በድምር ከተገኘው ገቢ በ8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ይበልጣል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here