ባሕር ዳር: ጥር 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ በመጀመሪያው ዙር 36 ቡድኖችን አሳትፎ ዛሬ ምሽት 5:00 በሚደረጉ 18 ጨዋታዎች ይጠናቀቃል።
ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ደረጃ የሚይዙ ቡድኖችም በቀጥታ ወደ ጥሎ ማለፉ ይገባሉ።
ከዘጠነኛ እስከ 24ኛ ደረጃን የሚይዙ ቡድኖች ደግሞ በእርስ በእርስ ጨዋታ ጥሎ ማለፉን የሚቀላቀሉ ይኾናል።
እስካሁን አርሰናል እና ባየርን ሙኒክ ከወዲሁ ጥሎ ማለፉን መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል።
ካይራት፣ ስሳቪያፕራግ፣ ቪላሪያል እና አይንትራፍራንክፈርት ከወዲሁ መሰናበታቸው ታውቋል።
ዛሬ ከሦስተኛ እስከ 32ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ቡድኖች ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ የሚያስችላቸውን ነጥብ ለማስመዝገብ ዛሬ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ።
ዛሬ ምሽት 5:00 የሚደረጉ ጨዋታዎች፦
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



