ባሕር ዳር: ጥር 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ባየር ሙኒክ እንግሊዛዊውን የ32 ዓመት አጥቂ ሃሪ ኬንን ውል ለማራዘም እየተነጋገረ መኾኑን የቡድኑ የስፖርት ዳይሬክተር ማክስ ኤበርል አስታውቀዋል።
ተጫዋቹ ለፓንች ኒውስ ፔፐር እንደገለጸው ባየር ሙኒክ በሁሉም ነገር ስለተመቼኝ ክለቡ ከፈለገኝ ውል የማላራዝምበት ምክንያት የለም ብሏል።
ሃሪ ኬን ባየር ሙኒክን የተቀላቀለው እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2023 ከቶትንሃም በአራት ዓመት ውል ነበር። ለዝውውሩም 100 ሚሊዮን ዩሮ ወጭ መኾኑ ይታዎሳል።
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



