ሲዳማ ቡና መሪነቱን ለማጠናከር ዛሬ ይጫወታል።

0
35
ባሕር ዳር: ጥር 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ17ኛው ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ሦስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
በ33 ነጥብ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና እና በ26 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ነገሌ አርሲ ይጫወታሉ። ጨዋታው ቀን 9:00 ላይ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይደረጋል።
በሌላ ጨዋታ ምሽት 12:00 ላይ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ኢትዮጵያ ቡና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይኾናል።
ኢትዮጵያ ቡና በሊጉ ካደረጋቸው ጨዋታዎች 19 ነጥብ በመያዝ 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ተጋጣሚው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደግሞ በ17 ነጥብ 15ኛ ላይ ተቀምጧል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም ቀን 9:00 ላይ ደግሞ ድሬዳዋ ከተማ ከሸገር ከተማ ይገናኛሉ። ሸገር ከተማ በ16 ነጥብ 17ኛ ሲኾን ድሬዳዋ ከተማ ደግሞ 19 ነጥብ በመያዝ 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here