ባሕር ዳር፡ ጥር 18/2018ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ 23ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ እንድ ጨዋታ ይደረጋል፡፡
ኤቨርተን ምሽት 5:00 ሰዓት ሊድስ ዩናይትድን ይገጥማል፡፡
ኤቨርተን በሊጉ ካደረጋቸው 22 ጨዋታዎች በዘጠኙ አሸንፎ፣ በአምስቱ አቻ ተለያይቶ፣ በስምንቱ ተሸንፎ እና 32 ነጥብ በመያዝ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ክለቡ ጨዋታውን ማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሰባት ከፍ እንዲያደርግ ያስችለዋል፡፡
ተጋጣሚው ሊድስ ዩናይትድ ከ22 ጨዋታዎች በስድሰቱ አሸንፎ፣ በሰባቱ አቻ በመለያየት እና በዘጠኙ ተሸንፎ 25 ነጥብ በመያዝ 16ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
ቡድኑ ጨዋታውን ድል ቢያደርግ ወደ ወራጅ ቀጣናው ተንሸራቶ እንዳይገባ ያግዘዋል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከ1995 ወዲህ በ25 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ተገናኝተዋል።
ኤቨርተን በስምንቱ በማሸነፍ የበላይ ነው። ሊድስ ኤቨርተንን ያሸነፈው በስድስት ጨዋታዎች ብቻ ነው። በ11 ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።
ሊጉን አርሰናል ይመረዋል። ማንቸስተር ሲቲ ይከተላል። አስቶን ቪላ በሦሥተኛነት ተቀምጧል።
ዌስት ሃም፣ በርንሌይ እና ዎልቭስ ደግሞ ወራጅ ቀጣናው ውስጥ ይገኛሉ።
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለ



