ባሕር ዳር: ጥር 17/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ቶትንሃም እና ሊቨርፑል በአንዲ ሮበርትሰን ዝውውር ዙሪያ እየተወያዩ ነው።
ቶትንሃም ተጫዋቹን ለማዛወር ከሊቨርፑል በኩል 5 ሚሊዮን ፓውንድ መጠየቁን የዘገበው ሜይል ነው።

አርሰናል ጁሊያን አልቫሬዝን ለማዛወር 80 ሚሊዮን ፓውንድ መጠየቁን ቢቢሲ ስፖርት አስነብቧል።

በርንማውዝ የ24 ዓመቱን የላዚዮ እና የግሪክ ግብ ጠባቂ ክሪስቶስ ማንዳስ በውሰት ውል ለማስፈረም መቃረቡን የዘገበው ፋብሪዚዮ ሮማኖ ነው።

ባርሴሎና ወጣቱን አጥቂ ዩሱፍ ራሱል ንዲጃይ ከቴራሳ አካዳሚ በይፋ ሊያስፈረም መኾኑን ያሁ ስፖርት አስነብቧል።