ባርሴሎና መሪነቱን ይረከብ ይኾን?

0
33
ባሕር ዳር: ጥር 17/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በስፔን ላሊጋ 21ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባርሴሎና በሪያል ማድሪድ የተነጠቀውን ደረጃ መመለስ የሚያስችለውን ውጤት ለማስመዝገብ ምሽት 12:15 ላይ ከኦቭዮዶ ጋር ይጫወታል።
ባርሴሎና ከ20 ጨዋታዎች 49 ነጥብ በመሠብሠብ በሪያል ማድሪድ በሁለት ነጥብ ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ቡድኑ በላሊጋው የደረጃ ሰንጠረዥ አናት ላይ ለመቀመጥ የዛሬውን ጨዋታ የግድ ማሸነፍ ይጠበቅበታል።
ተጋጣሚው ኦቭዮዶ ደግሞ በላሊጋው 20 ጨዋታዎችን አድርጎ 13 ነጥብ ብቻ በመያዝ በወራጅ ቀጣናው መጨረሻ ላይ ተቀምጧል።
ኦቭዮዶ እያሳየ ካለው ደካማ አቋም አንጻር ባርሴሎናን ይፈትነዋል ተብሎ አይጠበቅም።
በሌሎች የዛሬ የላሊጋው መርሐ ግብሮች ቀን 10:00 ላይ አትሌቲኮ ማድሪድ ከማዮርካ ይጫወታሉ።
ምሽት 2:30 ደግሞ ሪያል ሶሴዳድ ከሴልታቪጎ እንዲሁም ምሽት 5:00 ላይ አላቬስ ከቢትስ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይኾናሉ።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here