በፈረንሳይ ሊግ አንድ ፒኤስጂ የሊጉ መሪ ለመሆን ይጫወታል።

0
50
ባሕር ዳር: ጥር 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በፈረንሳይ ሊግ አንድ ዛሬ ምሽት 4:00 ፓሪስ ሴንት ዠርሜ መሪ ለመሆን የሚያስችለውን ነጥብ ለማስመዝገብ ከኦክሰር ጋር ይጫወታል።
ፓሪስ ሴንት ዠርሜ በሊጉ 18 ጨዋታዎችን በማድረግ 42 ነጥብ በመሠብሠብ በሁለተኛነት ተቀምጧል። የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ ነጥቡን 45 በማድረስ መሪ መኾን ያስችለዋል።
ኦክሰር ከ18 ጨዋታዎች 12 ነጥብ በመያዝ በወራጅ ቀጣና ውስጥ 17ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ቡድኑ የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ ከወራጅ ቀጣና እንዲወጣ እገዛው ከፍተኛ ነው።
ሁለቱ ቡድኖች እንደ አውሮፓ አቆጣጠር 2023 ወዲህ በ28 ጨዋታዎችን አድርገዋል። ፓሪስ ሴንት ዠርሜ በ15 ጨዋታዎች ሲያሸንፍ ኦክሰር ደግሞ በስድስት ጨዋታዎች አሸንፏል። በሰባት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።
በጣልያን ሴሪ ኤም ዛሬ ምሽት 4:45 ኢንተር ሚላን በሜዳው ከፒሳ ጋር ይጫወታል። ኢንተር ሚላን እስካሁን 21 ጨዋታዎችን አድርጎ በ16 ጨዋታዎች አሸንፎ በአንዱ አቻ ተለያይቶ እና በአራት ጨዋታዎች ተሸንፎ 49 ነጥብ በመሠብሠብ ሊጉን እየመራ ይገኛል።
ተጋጣሚው ፒሳ ደግሞ ከ21 ጨዋታዎች 14 ነጥብ በመያዝ ወራጅ ቀጣናው ውስጥ ይገኛል። ሁለቱ ቡድኖች እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከ2020 ወዲህ በ15 ጨዋታዎች ተገናኝተው ኢንተር በዘጠኝ ጨዋታዎች ሲያሸንፍ ፒሳ በሦስቱ አሸንፏል። በሦስት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።
በዛሬው ጨዋታ ኢንተር ሚላን መሪነቱን ለማጠናከር ፒሳ ደግሞ ከወራጅ ቀጣናው ለመውጣት የሚያግዘውን ነጥብ ለማስመዝገብ ጠንካራ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here