የዛሬ የአውሮፖ ሊግ ጨዋታዎች፦

0
42
ባሕር ዳር: ጥር 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የዮሮፖ ሊግ ሰባተኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ 18 ጨዋታዎችን በተለያዩ ከተሞች ያስተናግዳል።
የሊጉ መሪ የፈረንሳዩ ኦሎምፒክ ሊዮንስ ወደ ስዊዘርላንድ አምርቶ ያንግ ቦይስን ይገጥማል።
ኦሎምፒክ ሊዮንስ እስካሁን ስድስት ጨዋታዎችን አድርጎ በአምስቱ በማሸነፍ፣ በአንድ ጨዋታ ተሸንፎ እና 15 ነጥብ በመሠብሠብ ሊጉን በመምራት ላይ ይገኛል።
አንጻሩ ተጋጣሚው ያንግ ቦይስ ከስድስት ጨዋታዎች በሦስቱ አሸንፎ፣ በሦስቱ ተሸንፎ እና ዘጠኝ ነጥብ በመያዝ 21ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በዛሬው ጨዋታ ኦሎምፒክ ሊዮንስ ደረጃውን ለማስጠበቅ ያንግ ቦይስ ደግሞ ደረጃውን ከፍ ለማድረግ የሚያደርጉት ጨዋታ በመሆኑ ተጠባቂ ነው።
በስምንት ነጥብ 22ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የኖርዌዩ ብራን በ15 ነጥብ ሁለተኛ ከኾነው ከዴንማርኩ ሚድጄላንድ ጋር ይጫወታል።
ሚድጄላንድ መሪ ለመኾን ብራን ደግሞ ደረጃውን አሻሽሎ ወደ ቀጣዩ ዙር ለመግባት ጠንካራ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ተጠብቋል።
የቱርክየው ፊነርባቼ ከእንግሊዙ አስቶን ቪላ የሚያደርጉት ጨዋታም ተጠባቂ ነው።
አስቶን ቪላ ሦስተኛ ደረጃን የያዘ ሲኾን ፊነርባቼ ደግሞ 12ኛ ነው። ሁለቱ ቡድኖች ካላቸው ወቅታዊ አቋም አኳያ ዛሬ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ ነው የተባለው።
አራተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሪያል ቢትስ 18ኛ ላይ ከተቀመጠው ከግሪክ ፓኦክ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ሁሉም ጨዋታዎች ምሽት 2:45 ይካሄዳሉ።
በሌሎች የምሽት 2:45 ጨዋታዎች፦
👉 ቦሎኛ ከሴልቲክ
👉 ፌይኑርድ ከስቱርም ግራዝ
👉 ፍሬቡርግ ከማካቢ ቴላ ቪቭ
👉 ማልሞ ከሬድ ስታር ቤልግሬድ
👉 ቪክቶሪያ ፕላዛን ከፖርቶ ይጫወታሉ።
ምሽት 5:00 ደግሞ፦
👉 ሴልታ ቪጎ ከሊል
👉 ዳይናሞ ዛግሬብ ከኤፍሲኤስቢ
👉 ፌሬንቺቫሮስ ከፓናቲናይኮስ
👉 ናይስ ከጎ ኤሄድ ኤግልስ
👉 ሬንጀርስ ከሉዶጎሬትስ ራዝግራድ
👉 ሬድ ቡል ሳልዝቡርግ ከባሴል
👉 ሮማ ከስቱትግራት
👉 ስፖርቲንግ ብራኛ ከኖቲንግሃም ፎሬስት
👉 ዑልትሬች ከጌንክ የሚጫወቱ ይኾናሉ።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here