ባሕር ዳር: ጥር 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአውሮፓ ሻምፒዮን ሊግ ዛሬ ዘጠኝ ጨዋታዎችን ያስተናግዳል። ምሽት 5:00 የፈረንሳዩ ማርሴል ከእንግሊዙ ሊቨርፑል የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
ሁለቱ ቡድኖች እንደ አውሮፖ አቆጣጠር ከ2004 ዓ.ም ወዲህ በስድስት ጨዋታዎች ተገናኝተው ሊቨርፑል በሦሥት ጨዋታዎች በማሸነፍ የበላይ ነው። ማርሴል በሁለት ጨዋታ ሲያሸንፍ በአንድ ጨዋታ ደግሞ አቻ ነው የተለያዩት።
ማርሴል በፈረንሳይ ሊግ አንድ ሦሥተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ሊቨርፑል ደግሞ በፕሪሚየር ሊጉ አራተኛ ነው።
ቡድኖች በየሊጋቸው ካላቸው ወቅታዊ አቋም አንጻር ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ባለው የደረጃ ሰንጠረዥ ውስጥ ለመግባት ዛሬ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ተጠብቋል።
ጨዋታውን የሚያሸንፈው ቡድን ደረጃውን የሚያሻሽል ይኾናል። በሌላ የምሽት 5:00 ተጠባቂ ጨዋታ የጀርመኑ ባየርን ሙኒክ ከቤልጀየሙ ዩኒየን ሴንት ጊሎይሲ ጋር ይጫወታሉ።
ባየርን ሙኒክ በሻምፒዮንስ ሊጉ ከስድስት ጨዋታዎች 15 ነጥብ በመሠብሠብ ሦሥተኛ ነው። ቡድኑ የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ ያደርጋል።
ዩኒየን ሴንት ጊሎይሲ ደግሞ ከስድስት ጨዋታዎች ስድስት ነጥብ ብቻ የያዘ በመኾኑ በቀጥታ ወደ ቀጣዩ ዙር ጨዋታ ለማለፍ ዛሬ ማሸነፍ ይጠበቅበታል።
ምሽት 2:45 ደግሞ ጋላታሳራይ ከአትሌቲኮ ማድሪድ፣ ካራባግ ከኢንትራክት ፍራንክፈርት ይጫወታሉ።
በሌሎች የምሽት 5:00 ጨዋታዎች አታላንታ ከትሌቲክ ክለብ፣ ቼልሲ ከፓፎስ፣ ጁቬንቱስ ከቤኒፊካ፣ ኒውካስትል ዩናይትድ ከፒኤስቪ፣ ስላቫ ፕራግ ከባርሴሎና ይጫወታሉ።
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን



