ለአፍሪካ ዋንጫ ክብሯ ብሔራዊ በዓል አወጀች።

0
36

 

ባሕር ዳር፡ ጥር 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 35ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ትናንት ሲጠናቀቅ ሴኔጋል ሞሮኮን በተጨማሪ 30 ደቂቃ 1ለ0 አሸንፋ ሻምፒዮን ኾናለች።

ይህን ድል ተከትሎም ሴኔጋል ዕለቱ ብሔራዊ ክብረ በዓል ኾኖ እንዲከበር አውጃለች።

የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ ሀገሪቱ በአፍሪካ ዋንጫ ያስመዘገበችውን አስደናቂ ድል “ለብሔራዊ ኩራት ታሪካዊ ድል” ሲሉም አሞካሽተውታል።

ዕለቱም የሀገሪቱ ብሔራዊ በዓል ኾኖ እንዲከበር አውጀዋል።

ሴኔጋላዊያን ብሔራዊ ቡድኑ ሻምፒዮን ከኾነበት ሰዓት ጀምሮ ደስታቸውን ጎዳና ላይ ወጥተው በተለያዩ ሁነቶች እና ክዋኔዎች እያከበሩት ይገኛሉ።
በሙሉጌታ ሙጨ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here