የሊጉ 22ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ

0
46
ባሕር ዳር: ጥር 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 22ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ብራይተን ከቦርንማውዝ ምሽት 5:00 ሰዓት በሚያደርጉት ጨዋታ ይቋጫል።
ብራይተን በሊጉ 21 ጨዋታዎችን በማድረግ በ29 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በዛሬው ጨዋታ ካሸነፈም ደረጃውን የሚያሻሽል ይኾናል።
ተጋጣሚው ቦርንማውዝ እስካሁን ካደረጋቸው 21 ጨዋታዎች 26 ነጥብ በመያዝ 15ኛ ደረጃን ይዟል። ጨዋታውን ማሸነፍ ደረጃውን ከፍ እንዲያደርግ ያስችለዋል።
ሁለቱ ቡድኖች በቅርብ በተገናኙባቸው 26 ጨዋታዎች ቦርንማውዝ በ11 ጨዋታዎችን አሸንፏል።
ብራይተን በበኩል በ10 ጨዋታዎች አሸንፏል። በአምስት ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።
ቡድኖቹ ካላቸው ወቅታዊ አቋም አኳያ እና የጨዋታው አሸናፊም ደረጃን ከፍ ማድረግ ስለሚያስችል ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ቢቢሲ አስነብቧል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here