በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

0
46

 

ባሕር ዳር: ጥር 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 15ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምር ሊግ ጨዋታ ዛሬም ሲቀጥል አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ። ከእነዚህ ጨዋታዎች መካከል ፋሲል ከነማ ከሸገር ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

ፋሲል ከነማ በ14ኛ ሳምንት የሊጉ የደረጃ ሠንጠረዥ በ25 ነጥብ እና በአምስት የግብ ክፍያ ሦሥተኛ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው።

ፋሲል ከነማ ባለፈው የሊጉ ጨዋታ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ያደረገውን ጨዋታ የተሸነፈ ሲኾን ዛሬ ያለበትን ጨዋታ አሸንፎ ደረጃውን ለማሻሻል ነው ወደ ሜዳ የሚገባው።

ተጋጣሚው ሸገር ከተማ በ14 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ክለብ ነው። ሸገር ከተማ ባለፈው ሳምንት ከመቀለ 70 አንድርታ ጋር ያለግብ ተለያይቷል። ክለቡ በዛሬ ጨዋታው ፋሲልን እንደሚፈትን ነው የሚጠበቀው። ጨዋታውም ቀን 7፡00 ይካሄዳል።

በሊጉ ሌሎች ጨዋታዎችም ሲካሄዲ ነገሌ አርሲ ከወላይታ ዲቻ 9፡00፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 12፡00 እና ሀድያ ሆሳዕና ከምድረገነት ሽረ 10፡00 ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here