ኤሲ ሚላን ከኢንተር ሚላን ለመድረስ …

0
50
ባሕር ዳር: ጥር 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ኤሲ ሚላን ወደ መሪው ኢንተር ሚላን መጠጋት የሚያስችለውን ነጥብ ለማስመዝገብ ይጫወታል፡፡
በጣልያን ሴሪኤ 20ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ኮሞ እና ኤሲ ሚላን ምሽት 4:45 ይጫወታሉ፡፡
ኮሞ ከ19 ጨዋታዎች 34 ነጥብ በመሰብሰብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ነው። ተጋጣሚው ኤሲ ሚላን ደግሞ ከ19 ጨዋታዎች 40 ነጥብ በመሰብሰብ ሁለተኛ ነው። ጨዋታውን ካሸነፈም ነጥቡን 43 በማድረስ መሪው ኢንተር ሚላን እስኪጫወት ድረስ በነጥብ ይስተካከላል።
ሁለቱ ቡድኖች በቅርብ በሦስት ጨዋታዎች ተገናኝተዋል፡፡ ኤሲ ሚላን በሁሉም ጨዋታዎች ስድስት ግቦችን አስቆጥሮ አሸንፏል፡፡
ኮሞ ባለፉት ሦስት ጨዋታዎች ኤሲ ሚላን ማሸነፍ አልቻለም፡፡
በሌላ ጨዋታ ሄላስ ቬሮና ከቦሎኛ ምሽት 2:30 ይጫወታሉ፡፡
ሴሪኤውን ኢንተር ሚላን ሲመራው፣ ኤሲ ሚላን ይከተላል፡፡ ጁቬንቱስ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ፊዮሬንቲና፣ ሄላስ ቬሮናና ፒሳ ወራጅ ቀጣናው ውስጥ ይገኛሉ፡፡
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here