የአፍሪካ ዋንጫው ምርጦች

0
256

ባሕርዳር: የካቲት 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 34ተኛ የአፍሪካ ዋንጫ ብዙ የማይረሱ ትዝታዎችን ትቶ ኮትዷቯርን አንግሶ ተጠናቋል። በቡድን ደረጃ በውጣ ውረዶች የተንገላታው የአዘጋጇ ኮትዲቯር ቡድን በመጨረሻ ናይጀሪያን በማሸነፍ ለድል በቅቷል።

ከቡድን በተጨማሪም በግለሰብ ደረጃ በውድድሩ ምርጥ ብቃታቸውን ያሳዩ ተጫዋቾች እውቅና አግኝተዋል።በዚህ መሰረት የናይጀሪያው አምበል ዊልያም ትሮስት ኢኮንግ የውድድሩ ምርጥ ተጫዋች ኾኗል።

ይህ ተከላካይ መስመር ተጫዋች በውድድሩ ሦስት ግቦችን በማስቆጠር ሀገሩን ለፍጻሜ ለማብቃት ትልቅ ድርሻ ወስዷል።በፍጻሜውም የናይጀሪያን ብቸኛ ግብ ማስቆጠር ችሏል።
የኢኳቶሪያል ጊኒው ኢሚሊዮ ኑሲ ደግሞ የአፍሪካ ዋንጫው ኮከብ አግቢ ነው።ተጫዋቹ በአምስት ግቦች ነው የበላይ ኾኖ ያጠናቀቀው።

ደቡብ አፍሪካ የውድድሩን ሦስተኛ ደረጃ ይዛ ማጠናቀቋ ይታወሳል።ለዚህ እንድትበቃ የግብ ጠባቂዋ ሮንዊን ዊሊያምስ ብቃት ድንቅ ነበር።የቡድኑ አምበል ኾኖ ቡድኑን በተሻለ ከመምራት በተጨማሪ ድንቅ ብቃቱን በውድድሩ አሳይቷል።በዚህም የውድድሩ ምርጥ ግብ ጠባቂ ኾኗል።

በአስማማው አማረ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here