የቪዲዮ ረዳት ዳኝነት (ቫር) ስህተቶች፦

0
11
ባሕር ዳር: ጥር 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በሚደረጉ ጨዋታዎች የቪዲዮ ረዳት ዳኝነት (ቫር) ስህተት እየጨመረ መጥቷል፡፡
ቢቢሲ ስፖርት በሠበሠበው መረጃ መሠረት በፕሪምየር ሊጉ ከተደረጉ 19 ጨዋታዎች በቪዲዮ ረዳት ዳኝነት ስህተት ምክንያት ተጫዋቾች ያላግባብ የቀይ ካርድ ሰለባ በመኾን ቡድኖች ሲጎዱ ተስተውለዋል፡፡
በቫር እና በአተረጓጎም ስህተትም ከጨዋታ ውጭ የነበሩ የጨዋታ ሂደቶች እንዳልነበሩ ተቆጥረው ግቦች እንዲመዘገቡ መደረጋቸውም ተነግሯል፡፡
በቢቢሲ የጨዋታ ንጽጽር መሠረትም በ2024/25 የውድድር ዘመን ከተደረጉ 19 ጨዋታዎች የተመዘገበው የቪዲዮ ረዳት ዳኝነት ስህተት 10 ነበር፡፡
የተለያዩ ቡድኖችም በወቅቱ በቪዲዮ ረዳት ዳኝነት በሚፈጠሩ ስህተቶች መጎዳታቸውን ጠቅሰው አወዳዳሪው አካል አሠራሩን መለስ ብሎ እንዲፈትሽ መጠየቃቸው አይዘነጋም፡፡
የቡድኖች ቅሬታ ሳይፈታ ዘንድሮም ስህተቶች መጨመራቸውን ነው ዘገባው ያመላከተው፡፡
በ2025/26 የውድድር ዘመን እስከ 19ኛ ሳምንት የሊጉ ጉዞ 13 የቪዲዮ ረዳት ዳኝነት ስህተቶች መመዝገባቸውን ቢቢሲ ስፖርት አትቷል፡፡
በርንማውዝ፣ ብሬንትፎርድ እና ማንቸስተር ዩናይትድ ሁለት ጊዜ በቪዲዮ ረዳት ዳኝነት በተፈጠረ ስህተት ማግኘት የነበረባቸውን ነጥብ ተነፍገዋል ነው የተባለው፡፡
ብራይተን፣ ክሪስታል ፓላስ፣ ኤቨርተን፣ ፉልሃም፣ ሊቨርፑል፣ ማንቸስተር ሲቲ እና ወልቨስ በቪዲዮ ረዳት ዳኝነት ስህተት አንዳንድ ጊዜ ማግኘት የነበረባቸውን ነጥብ ማጣታቸው ተነግሯል፡፡
የቪዲዮ ረዳት ዳኝነት (ቫር) ስህተት ከመቀነስ ይልቅ በየጊዜው እየጨመረ እና የቅሬታ ምንጭ እየሆነም ቀጥሏል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here