ማን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ይኾናል?

0
8
ባሕር ዳር: ጥር 04/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ተፋላሚዎችን ለይቷል። በዚህ ሂደት ግብ በማስቆጠር ለቡድናቸው አስተዋጽኦ ከማድረግ በተጨማሪ የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ለመሆን አድል ያላቸው ተጫዋቾች አሉ።
ሞሮኳዊው ብራሂም ዲያዝ አምስት ግቦችን በማስቆጠር በግንባር ቀደምትነት ስሙ ሰፍሯል፡፡ ተጨዋቹ ሀገሩ ቀጣይ ጨዋታዎች ስለሚኖራት ተጨማሪ ግቦችን በማስቆጠር የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ ለመጨረስ ቀዳሚ ግምት አግኝቷል።
ናይጄሪያዊ ቪክቶር ኦሲምሄን እና ግብጻዊው ሞሐመድ ሳላህም አራት አራት ግቦችን በማስቆጠር ለኮከብ ግብ አግቢነት እየተፎካከሩ ነው።
የሞሮኮው አጥቂ አዩብ ኤል ካቢ እና ናይጄሪያው አዴሞላ ሉክማንም የሦስት ግቦች ባለቤት በመኾናቸው በተጨማሪ ጨዋታዎች ተጨማሪ ግቦችን የማስቆጠር ዕድል አላቸው። በመሆኑም ከፍተኛ ግብ አግቢ ሆኖ የመጨረስ እድል አላቸው።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here