ባሕር ዳር: ጥር 04/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በስፔን ሱፐር ካፕ ፍጻሜ ባርሴሎና ሪያል ማድሪድን ማሸነፍ ችሏል።
ባርሴሎና ሪያል ማድሪድን ማሸነፍ የቻለው 3ለ2 በኾነ ውጤት ነው።
በሳዑዲ አረቢያ በተካሄደው ኤልክላሲኮ የፍጻሜ ጨዋታ የማሸነፊያ ግቦችን ሁለቱን ራፊንሃ እና አንዷን ደግሞ ሮቤርቶ ሌቫንዶቭስ ለባርሴሎና አስቆጥረዋል።
ቪኒሺየስ ጁኒየር እና ጎንዛሎ ጋርሺያ ደግሞ ማድሪድን ከሽንፈት ያልታደጉ ግቦች አስቆጥረዋል፡፡
በዚህ ጨዋታ የባርሴሎናው ጆንግ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተወግዷል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



