ባሕር ዳር: ጥር 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የ2026 የሴቶች ከ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ድልድል ይፋ ሲኾን ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን ጋር ተደልድላለች።
ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ኢትዮጵያ የመጀመርያውን ዙር ካለፈች በሁለተኛ ዙር የማላዊ እና ቡሩንዲን አሸናፊ ትገጥማለች።
ጨዋታውም የመጀመርያ ዙር ሚያዚያ ላይ ሲደረግ ሁለተኛ ዙር ግንቦት ላይ ሦስተኛ ዙር ሰኔ ወይም ሐምሌ ላይ ሊደረግ እንደሚችል የወጣው መርሐግብር አመላክቷል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



