ደብረ ብርሃን ከተማ ዛሬ ደረጃውን ለማሻሻል ይጫወታል።

0
7
ባሕር ዳር: ጥር 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በምድብ “ለ” የ11ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የአማራ ክልል ተወካዩ ደብረ ብርሃን ከተማ ዛሬ በጅማ ስታዲየም ከመንጌ ቤላሻንጉል ጋር ይጫወታል።
ጨዋታው ቀን 7:00 ላይ ይደረጋል።
ደብረ ብርሃን ከተማ ከጨዋታ ጨዋታ አቋሙን እያሻሻለ ይገኛል። ከነበረበት 11ኛ ደረጃ ነጥቡን ከፍ በማድረግም አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ቡድኑ የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈም ደረጃውን ከፍ በማድረግ ወደ መሪ ቡድኖች መጠጋት ያስችለዋል።
በዚሁ ምድብ ቀን 9:30 ላይ ቦዲቲ ከተማ ከሶሎዳ ዓድዋ ጋር ይጫወታሉ።
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የምድብ “ለ”ን ሀላባ ከተማ በአንደኛነት እየመራው ይገኛል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here