ደብረ ብርሃን፡ ጥር 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ታላቁ ሩጫ በደብረ ብርሃን ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የስፖርት ቱሪዝምን ለማጠናከር የተዘጋጀ መርሐግብር ነው።
በአትሌቶች የ6 ኪሎ ሜትር ውድድር በሁለቱም ጾታዎች ተካሂዷል።
በወንዶች ስጦታው ሰማኸኝ ከደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ ቀዳሚ ሆኖ አጠናቅቋል። ቦጋለ በየነ እና አየለ ከበደ ከደብረብርሃን አትሌቲክስ ማሠልጠኛ ሁለተኛና ሦስተኛ ኾነው ገብተዋል።
በሴቶች የአዋቂ ዘርፍ ደግሞ አማረች ገብሬ፣ ደመቅ ጥላሁ እና የዘብነሽ ወንዴ ከደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ ከአንድ እስከ ሦስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
በሁለቱም ጾታ ከ16 ዓመት በታችና ከ12 ዓመት በታች ታዳጊዎች ውድድርም እየተካሄደ ነው። የማራቶን እና የአዋቂዎች የሩጫ ውድድርም በዛሬው ዕለት ይካሄዳሉ።
“ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ” በሚል ሀገርን በሩጫ ስፖርት አማካኝነት የማሰስ እና የማስተዋወቅ ዓላማ ያለው ውድድሩ የዛሬውን ጨምሮ በስድስት የሀገሪቱ የክልል ከተሞች የሚደረግ ይሆናል።
ዘጋቢ፦ ደጄኔ በቀለ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



