ባሕር ዳር: ጥር 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ፖርቱጋላዊውን አሠልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆን “በእግር ኳስ ውጤታማው አሠልጣኝ” የሚሏቸው ጥቂት አይደሉም።
በሌላ ወገን ሰውየው በሚሰጡት ሃሳብ ተነስተው “አወዛጋቢው” የሚል ቅጽል የሰጧቸውም ከአድናቂዎቻቸው የማይተናነሱ ናቸው።
ጆዜ እንደ አውሮፖውያን አቆጣጠር በ2000 በቤኒፋካ አሠልጣኝነትን ጀምረው በፖርቶ፣ ቼልሲ፣ ኢንተር ሚላን፣ ሪያል ማድሪድ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ፣ ቶትንሃም፣ ሮማ፣ ፊነርባቼ አሁን ደግሞ ቤኔፊካን እንደገና እያሠለጠኑ ነው።
አመላቸው እያኮራም የሚባሉት ፖርቱጋላዊ አሠልጣኝ በቅርቡም በቤኔፊካ የቡድን አባላት ያልተወወደ አስተያየት ሰጥተዋል።
ቤንፊካ በፖርቱጋል ሊግ ካፕ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በብራጋ 3ለ1 ተሸንፎ ከውድድሩ ውጭ ሆኗል። ይሄን ተከትሎ
ተጫዋቾች እንቅልፋቸውን ከመተኛት ይልቅ ስለ ሽንፈቱ ምክንያት ማሰብ አለባቸው ማለታቸውን ዘ ጋርድያን ዘግቧል።
ይህ ሃሳባቸውም የክለቡ ኅላፊዎች እና ተጫዋቸችን አስቆጥቷል ተብሏል።
የቤኔፊካ ክለብ ኅላፊዎችም ሞሪንሆን በሌላ አሠልጣኝ ለመተካት እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ደይሊ ሜል አስነብቧል።
በቅርቡ ከዩናይትድ የተባረሩት አሞሪም ደግሞ ቀዳሚ ተመራጭ ናቸው ተብሏል። አሞሪም በኦልድትራፎርድ ባይሳካላቸውም በስፖርቲንግ የነበራቸው ስኬታማነት ሞሪንሆን ለመተካት ተመራጭ አድርጓቸዋል።
አሞሪም ከሞሪንሆ በተሻለ ዘመናዊ አጨዋወትን ይተገብራሉ የሚለው የቤኔፊካ ክለብ መሪዎች እይታ ሌላው ሞሪንሆን መተካት ለሚለው ሃሳብ ምክኒያት መሆኑም ተነስቷል።
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



