ስፖርት ለቱሪዝም ዘርፉ ተመራጭ መንገድ ነው።

0
8

ደብረብርሃን: ጥር 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ታላቁ ሩጫ በደብረ ብርሃን ከተማ ጥር 3/2018 ዓ.ም ይካሄዳል። በስፍራው የደረሱ ተሳታፊዎችም በአንኮበር ቤተ መንግሥት ጉብኝት አድርገዋል።

ታላቁ ሩጫ ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የስፖርት ቱሪዝምን ለማጠናከር የተዘጋጀ መርሐግብር ነው።

በቱሪዝም ሚኒስቴር ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አልቃድር አሕመድ የሩጫ ዓላማው የስፖርት ቱሪዝምን ማስፋት መኾኑን ገልጸዋል።

በየትኛውም ሁኔታ አንድ ሰው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ከተንቀሳቀሰ የቱሪዝም ጉብኝት ዘርፉን ያሰፍዋል፤ ስፖርት ደግሞ አንዱ ተመራጭ መንገድ ነው ብለዋል።

የስፖርት ቱሪዝም በተለያዩ ክልሎች እየተተገበረ መኾኑ ደግሞ ቱሪዝሙን ያነቃቀዋል ነው ያሉት።

“ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ” በሚል ሀገርን በሩጫ አማካኝነት የማሰስ እና የማስተዋወቅ ዓላማን ያነገበ በተከታታይ በስድስት የክልል ከተሞች ይደረጋል ነው የተባለው።

የታላቁ ሩጫ የኮሙኒኬሽን ኀላፊ ሐና ገብረሥላሴ በውድድሩ ከ3ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ይሳተፉሉ ብለዋል።
በውድድሩ አትሌቶች እና ታዳጊ ሕጻናት እንደሚሳተፉ አመላክተዋል።

ዘጋቢ፦ወንዲፍራ ዘዉዴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here