ባሕር ዳር: ጥር 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ማንቸስተር ሲቲ ጋናዊውን አንቶኒ ሴሜንዮን ከቦርንማውዝ በ65 ሚሊዮን ፓውንድ አስፈርሟል።
የዝውውር የገንዘብ መጠኑ በቦርንማውዝ ቡድን ታሪክ ውዱ ሽያጭ ነው ተብሏል።
ዝውውሩ ተጫዋቹን በማንቸስተር ሲቲ እ.አ.አ እስከ 2031 ድረስ የሚያቆየው ይኾናል።
የ26 ዓመቱ ተጫዋች የቀድሞው የማንቸስተር ሲቲ ተጫዋች የነበረው ያያ ቱሬ ይለብስ የነበረውን የ42 ቁጥር መለያ ለብሶ የሚጫወት መኾኑን ቢቢሲ አስነብቧል።
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



