አጫጭር የዝውውር ዜናዎች፦

0
13
ባሕር ዳር: ጥር 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) አርሰናል የ25 ዓመቱን እንግሊዛዊ የክሪስታል ፓላስ ተከላካይ ማርክ ጉሂን የቡድኑ አካል ለማድረግ በጥብቅ መፈለጉን አስታውቋል።
ማንቸስተር ሲቲ ደግሞ በሚቀጥሉት ቀናት ማርክ ጉሂን እንደሚያስፈርመው እርግጠኛ መኾኑን ሚረር አስነብቧል።
👉 ቶተንሃም የ19 ዓመቱን ብራዚላዊ ተከላካይ ሱዛንን ከሳንቶስ ቡድን ላይ ለማዘዋወር ከተጫዋቹ ጋር በግል ጉዳዮች ዙሪያ መስማማታቸውን ቢቢስ አስነብቧል።
👉 ዎልቭስ እንግሊዛዊውን ወጣት ኢንተርናሽናል ማትየስ ማኔን በቡድን ስብስቡ ውስጥ ለማካተት ቁርጠኛ ስለመኾኑ የዘገቡት ሜይል እና ሚረር ናቸው።
👉 የ26 ዓመቱ ግብጻዊ አጥቂ ኦማር ማርሙሽ በጥር ወር ከማንቸስተር ሲቲ የመልቀቅ እቅድ የለውም መባሉን ቢቢሲ ነው የዘገበው።
👉 በሌላ የተያያዘ ዜና ማንቸስተር ሲቲ የ21 ዓመቱን ጣልያናዊ የቀኝ መስመር ተከላካይ ማይክል ካዮዴ ለማስፈረም መቋመጣቸውን አስታውቀዋል።
👉 ሪያል ማድሪድ አንቶኒዮ ሩዲገርን በዚህ የዝውውር ወቅት በ10 ሚሊዮን ዩሮ ለመሸጥ እንደሚፈልግ አስታውቋል።
የተጫዋቹ የቀድሞ ቡድን ቼልሲ እና ፓሪስ ሴንት ዠርሜይን ለማስፈረም ፍላጎት ማሳየታቸው ተዘግቧል።
👉 አስቶንቪላ የ16 ዓመቱን ብሪያን ማጅን ከሜይንዝ ቡድን ላይ በ10 ሚሊዮን ፓውንድ ለማስፈረም መስማማቱን ቢቢሲ አስነብቧል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here