ኤሲሚላን ወደ መሪው የሚጠጋበትን ነጥብ ለማስመዝገብ ይጫወታል።

0
12
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የጣልያን ሴሪኤ 19ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት ሁለት ጨዋታዎችን ያስተናግዳል።
ምሽት 4:45 ኤሲ ሚላን በሜዳው ጅኖዋን የሚጋብዝበት ጨዋታ ተጠባቂ ኾኗል።
ኤሲ ሚላን በሴሪኤው ካደረጋቸው 17 ጨዋታዎች 38 ነጥብ በመሠብሠብ ከመሪው ኢንተር ሚላን በአራት ነጥብ ዝቅ ብሎ በሁለተኛነት ተቀምጧል።
ቡድኑ ከ17 ጨዋታዎች የተሸነፈው በአንድ ጨዋታ ብቻ መኾኑ የቡድኑን ጥንካሬ ያሳያል።
ኤሲ ሚላን የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ ከኢንተር ሚላን ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አንድ ማጥበብ እና ይበልጥ የዋንጫው ተፎካካሪ ለመኾን ያስችለዋል። በመኾኑም ኤሲ ሚላን ለማሸነፍ ብርቱ ጨዋታ ያደርጋል ተብሎ ተጠብቋል።
ተጋጣሚው ጅኖዋ ከ18 ጨዋታዎች 15 ነጥብ ብቻ በመያዝ በወራጅ ቀጣናው ውስጥ ከሚገኙ ቡድኖች አናት ይገኛል። ጨዋታውን ማሸነፍ ከወራጅ ሥጋት እንዲርቅ ስለሚያደርገው ጠንካራ ጨዋታ ያደርጋል ሲል ማርካ አስነብቧል።
በሌላ የዛሬ ምሽት 2:30 ጨዋታ ክሬሞንሴ ከካግሊያሪ የሚያደርጉት ጨዋታ የደረጃ ለውጥ የሚያስከትል መኾኑንም ቢቢሲ ስፖርት አስነብቧል።
ሴሪኤውን ኢንተር ሚላን በመምራት ላይ ይገኛል። ኤሲ ሚላን በሁለተኛነት ሲከተል ናፖሊን በሦሥተኛነት ደረጃ ተቀምጧል
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here