ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በስፔን ሱፐርኮፓ ጨዋታ አትሌቲኮ ማድሪድ ከሪያል ማድሪድ ምሽት 4:00 ላይ በግማሽ ፍጻሜ ዛሬ አጓጊ እና ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋሉ።
ሪያል ማድሪድ በላ ሊጋው መርሐ ግብር 19 ጨዋታዎችን አድርጎ 45 ነጥብ በመሠብሠብ በሁለተኛነት ሲቀመጥ አትሌቲኮ ማድሪድ ደግሞ ከ19 ጨዋታዎች 38 ነጥብ በመያዝ አራተኛ ደረጃን ይዞ ይገኛል።
ሁለቱ ቡድኖች እንደ አውሮፖ አቆጣጠር ከ2003 ወዲህ በ70 ጨዋታዎች ተገናኝተው ሪያል ማድሪድ በ32 ጨዋታዎች በማሸነፍ የበላይነቱን አሳይቷል።
አትሌቲኮ ማድሪድ ማሸነፍ የቻለው በ15 ጨዋታዎች ነው። በ23 ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።
ሁለቱ ቡድኖች በላ ሊጋው ካላቸው የደረጃ መቀራረብ እና ከወቅታዊ አቋማቸው አኳያ ዛሬ የሚያደርጉት የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ በእጅጉ ተጠባቂ ኾኗል።
ትናንት ባርሴሎና አትሌቲክ ክለብን 5ለ0 በማሸነፍ ለፍጻሜ መድረሱ ይታወሳል።
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



