ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የክሪስታል ፓላስ አሰልጣኝ ኦሊቨር ግላስነር ቡድኑ የቆረጠውን ዋጋ የሚደፍር ቡድን ከመጣ አምበሉን ማርክ ጉሂን በዚህ የተጫዋቾች የዝውውር ወቅት ለመሸጥ መወሰኑን ለቢቢሲ ስፖርት ተናግረዋል።
ማርክ ጉሂ ከክሪስታል ፓላስ ጋር ያለው ውል በቅርቡ እንደሚቋጭ ቡድኑ አስታውቋል።
ይህን ተከትሎም ማንቸስተር ሲቲ እና ሌሎች ቡድኖች ተጫዋቹን ለማስፈረም ተፎካካሪ ኾነው ብቅ ማለታቸውን ነው አሠልጣኝ ኦሊቨር ግላስነር የተናገሩት።
ጉሂ ክሪስታል ፓላስን የተቀላቀለው እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2021 እጅግ ውድ በተባለ 18 ሚልዮን ፓውንድ መኾኑ ይታዎሳል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



