ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጨዋታ ምሽት 4፡00 ነው የሚካሄደው። አሸናፊው ቡድንም ዋንጫውን ለማግኘት ይጫወታል።
ባርሴሎና በሊጉ እያሳየ ባለው ጥሩ አቋም የተሻለ ቢኾንም አትሌቲክ ቢልባኦ በዋንጫ ውድድሮች ላይ ጠንካራ ተቀናቃኝ በመኾኑ ጨዋታው አጓጊ እንደሚኾን ይጠበቃል።
ባርሴሎና በቅርብ ካደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ግስጋሴውን የቀጠለ ሲኾን ዛሬ ይህ ግስጋሴ በአትሌቲክ ቢልባኦ ይቆማል ወይስ የሚለውም የሚጠበቅ ነው።
በአንጻሩ አትሌቲክ ቢልባኦ ወጣ ገባ የኾነ አቋም እያሳየ የሚገኝ ቡድን ነው። በቅርቡም ካደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች በአንዱ ከማሸነፍ ውጭ በሌሎች አቻ እና ሽንፈትን ያስተናገደ ቡድን ነው።
ሁለቱ ቡድኖች እስካሁን 84 ጊዜ ተገናኝተው 54 ጊዜ ባርሴሎና በማሸነፍ ይመራል።
አትሌቲክ ቢልባኦም 14 ጊዜ ድል ቀንቶታል ቀሪው ጨዋታ ግን በአቻ ውጤት የተጠናቀቀ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



