በአፍሪካ ዋንጫ ሁለት የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ።

0
33
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ ምሽት ሞሮኮ ከታንዛንያ፣ ደቡብ አፍሪካ ከካሜሩን ወሳኝ ጨዋታዎችን ያደርጋሉ።
ምሽት 1:00 አዘጋጇ ሞሮኮ ከምሥራቅ አፍሪካ ተወካይ ታንዛንያ በስታዲ ልዑል ሙላይ አብደላህ ስታዲየም ይጫወታሉ።
ሁለቱ ሀገራት እንደ አውሮፖ አቆጣጠር ከ2010 ወዲህ በስምንት ጨዋታዎች ተገናኝተዋል። ሞሮኮ በሰባት ጨዋታዎች በማሸነፍ የበላይ ናት። ታንዛንያ ሞሮኮን ያሸነፈችው በአንድ ጨዋታ ብቻ ነው።
ሁለቱ ሀገራት ባደረጓቸው ያለፉት ስምንት ጨዋታዎች ሞሮኮ 15 ግብ ስታስቆጥር ታንዛንያ ያስቆጠረችው ግብ አምስት ብቻ ነው።
ሞሮኮ በዚህ አፍሪካ ዋንጫ ካደረገቻቸው ሦሥት ጨዋታዎች በሁለቱ አሸንፋ በአንዱ አቻ በመለያዬት ሰባት ነጥብ እና አምስት ንጹህ የግብ ክፍያ በመያዝ ምድቡን በአንደኝነት በመምራት ነው ለጥሎ ማለፉ የደረሰችው።
እንደ የሪያልማድሪዱ ብራሂም ዲያዝ፣ የሮማው ኒያል አል አይናኡይ፣ የማንቸስተር ዩናይትዱ ኑሴየር ማዝራዊ፣ የሪያል ቢትሱ ሶፍያን አምራባት የመሳሰሉ ክዋከብት በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ተካተዋል።
ሞሮኮ በሜዳዋ እና በደጋፊዎቿ ታግዛ እንደ መጫወቷ ታንዛንያን በቀላሉ ትረታታለች የሚሉ በርካታ ናቸው።
ምሥራቅ አፍሪካዊቷ ታንዛንያ ካደረገቻቸው ሦሥት ጨዋታዎች በሁለቱ አቻ በመለያዬት እና ሁለት ነጥብ በያዝ ጥሩ ሦሥተኛ ኾና ነው ያለፈችው።
አብዛኞቹ የታንዛንያ ተጫዋች በሀገር ውስጥ ሊግ የሚጫወቱ ሲኾኑ በአዛርባጃን የሚጫወቱት ፊሳል ሳሉም እና ማሳንኛ፣ በፈረንሳይ ሊግ ዋን ለ ሀቨር ቡድን የሚሰለፈው መብዋና ሳማታን በጨዋታው በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ አካታለች።
በሌላ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ምሽት 4:00 በአል መዲና ስታዲየም ደቡብ አፍሪካ እና ካሜሩን ይጫወታሉ።
ሁለቱ ሀገራት ከ2008 ወዲህ በአራት ጨዋታዎች ተገናኝተው ደቡብ አፍሪካ በአንድ ጨዋታ በማሸነፍ የበላይነቱን ይዛለች። በሦሥት ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።
ባፋና ባፋናዎቹም ኾኑ የማይበገሩት አናብስት በርካታ ስመ ጥር ፕሮፌሽናል ተጫዋቾችን በመያዛቸው የዛሬው ጨዋታ የቴክኒክ፣ የታክቲክ እና የሥነ ልቦና ብልጠት ይስተዋልበታል ተብሎ ተጠብቋል ሲል ዴይሊ ሜይል አስነብቧል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here