ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት ዛሬ ፋሲል ከነማ ከአዳማ ከተማ ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም ያደረገውን ጨዋታ ያለምንም ግብ ተለያይቷል።
በሊጉ አንድም ጨዋታ ያልተሸነፈው ፋሲል ከነማ ዛሬም ያለመሸነፍ ጉዞውን አስቀጥሏል። ነገር ግን ነጥብ በመጣሉ ቢያንስ ለጊዜው ሊጉን የሚመራበትን እድል አባክኗል።
ቡድኑ በመሪው ሲዳማ ቡና በግብ ክፍያ ተበልጦ በ25 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
ዘጋቢ፦ ሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



