አጫጭር የዝውውር መረጃዎች።

0
37
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ስመ ጥር የዓለማችን የእግር ኳስ ቡድኖች በጥር ወር የተጫዋቾች የዝውውር ገበያ በንቃት እና በስፋት እየተሳተፉ እንደሚገኙ ቢቢሲ የተለያዩ የመረጃ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።
👉የሪያል ማድሪዱ የክንፍ መስመር ተጫዋች ሮድሪጎ በአርሰናል፣ በማንቸስተር ሲቲ እና በሊቨርፑል እየተፈለገ የሚገኝ ተጫዋች መኾኑን አስ – ስፓኒሽ አስነብቧል።
👉ማንቸስተር ዩናይትድ የብራይተኑን ካሜሩናዊ የ21 ዓመት ካርሎስ ባሌባን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይቷል ያለው ስካይ ስፖርት ነው።
👉ዌስትሃም ዩናይትድ የ27 ዓመቱን አጥቂ ታቲ ካስቴላኖስን በ25 ሚሊዮን ፓውንድ ለማስፈረም ትኩረት አድርጓል።
👉ሊቨርፑል፣ ማንቸስተር ዩናይትድ እና ኒውካስትል የዋትፎርዱን ሞሮኳዊ የፊት መስመር አጥቂ ኦዝማኔ ማዓማዓ ላይ ዐይናቸውን ጥለውበታል።
👉ክሪስታል ፓላስ፣ ሊድስ ዩናይትድ እና ኖቲንግሃም ፎረስት የ26 ዓመቱ እንግሊዛዊ አማካኝ ጆ ዊሎክን ለማስፈረም ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።
👉ፉልሃም የ22 ዓመቱን አሜሪካዊ አጥቂ ሪካርዶ ፔፒን ከፒኤስቪ ለማስፈረም ያደረጉት ጥረት ሳንካ ገጥሞታል ሲል ዘ ሰን አስነብቧል።
ዘጋቢ፦ ሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here