ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 👉ሊቨርፑል በቤልጅየሙ ክለብ ብሩጅ የሚጫወተውን የ21 ዓመት ኢኳዶራዊ ተከላካይ ጆኤል ኦርዶኔዝን በ43 ሚሊዮን ፓውንድ ለማዛውር ፍላጎት ማሳየቱን ሚረር አስነብቧል፡፡
👉 ሮማ የሊቨርፑሉን የ33 ዓመት ግብፃዊ ተጫዋች ሞሐመድ ሳላህን በድጋሚ ለማስፈረም መጓጓቱን ላ ሪፐብሊካ-ኢን ኢታሊያን ዘግቧል፡፡
👉 ማንቸስተር ዩናይትድ በክሪስታል ፓላስ የሚጫወተውን የ28 ዓመት ፈረንሳዊ አጥቂ ዣን ፊሊፕ ማቴታ እና የሬኔሱን የ20 ዓመት ፈረንሳዊ ተከላካይ ጄረሚ ዣኬትን ለማስፈረም አቅዷል ሲል ስካይ ስፖርትስ አስነብቧል፡፡
👉 ማንቸስተር ዩናይትድ የ31 ዓመቱን ፖርቱጋላዊው አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝን ለመሸጥ ማሰቡን ከእግር ኳስ ውስጥ አዋቂዎች ማስማቱን ቢቢሲ አስፍሯል፡፡ ማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋቹን ከፖርቱጋሉ ስፖርቲንግ ሊዝበን ለማዛወር 80 ሚሊዮን ዩሮ ወጭ ማድረጉ ይታዎሳል፡፡
👉 ዌስትሃም የ29 ዓመቱን ስፔናዊው የክንፍ መስመር ተጫዋች አዳማ ትራኦሬን ለማስፈረም ፍላጎት ማሳደሩን ቴሌግራፍ መረጃውን አጋርቶታል፡፡
👉 ሪያል ማድሪድ 46 ሚሊዮን ዩሮ ወጭ ያደረገበትን ብራዚላዊው አጥቂ የቪኒሲየስ ጁኒየርን ውል ለማራዘም ውይይቱን እንደሚቀጥል አስ ኢን ስፓኒሽ ነው ያስነበበው።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



