የሴሪ ኤ ወሳኝ ጨዋታ

0
44

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በጣልያን ሴሪ ኤ ዛሬ ኤሲ ሚላን እና ካግሊያሪ ምሽት 4:45 ወሳኝ ጨዋታ ያደርጋሉ።

ኤሲ ሚላን በሴሪ ኤው 16 ጨዋታዎችን አድርጎ በ10 ጨዋታዎች አሸንፏል። በአምስት ጨዋታዎች አቻ ተለያይቷል። በአንድ ጨዋታ ደግሞ ተሸንፏል። 14 ንጹህ የግብ ክፍያ በመያዝ እና 35 ነጥብ በመሰብሰብ በደረጃ ሰንጠረዡ በሁለተኛነት ተቀምጧል።

ዛሬ ኤሲ ሚላን ካሸነፈ ነጥቡን 38 በማድረስ የሴሪ ኤው መሪ ይኾናል።

ተጋጣሚው ካግሊያሪ እስካሁን 17 ጨዋታዎችን አድርጎ እና 18 ነጥብ በመያዝ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ቡድኑ ጨዋታውን ካሸነፈ ደረጃውን የሚያሻሽል ይኾናል።

ሁለቱ ቡድኖች እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከ2004 ወዲህ በ39 ጨዋታዎች ተገናኝተው ኤሲ ሚላን በ39 ጨዋታዎች በማሸነፍ የበላይ ነው።

ካግሊያሪ ኤሲ ሚላንን ያሸነፈው በአንድ ጨዋታ ብቻ ነው። በስምንት ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።

ሴሪኤውን ኢንተር ሚላን በ36 ነጥብ እየመራው ይገኛል። ኤሲ ሚላን በ35 ነጥብ ይከተላል። ናፖሊን ደግሞ በ34 ነጥብ በሦስተኛነት መቀመጡን ቢቢሲ ዘግቧል።

በሙሉጌታ ሙጨ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here