“የምንጫወተው የሀገሪቱን ሰላም ለመመለስ ነው” የሱዳን ተጫዋቾች

0
31
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ አራት ወሳኝ ጨዋታዎችን ያስተናግዳል።
ምድብ አምስት ላይ በጦርነት እየተናጠች የምትገኘው ምሥራቅ አፍሪካዋ ሀገር ሱዳን ምሽት1:00 ላይ ቡርኪናፋሶን ትገጥማለች። ሱዳን በጦርነት ምክንያት መሠረተ ልማቷ እየፈረሰ፣ ሕዝቧ በረሃብ አለንጋ እየተሰቃየ በመኾኑ የእግር ኳስ ቡድኖቿ ጨዋታ እያደረጉ የሚገኙት በብዙ ፈተና ውስጥ ኾነው ነው።
ብሔራዊ ቡድኑም ለአፍሪካ ዋንጫ የደረሰው ከፍተኛ መስዋትነት በመክፈል በውጭ ሀገር ስታዲየሞች ተጫውቶ ነው። “የሱዳን ተጨዋቾች የምንጫወተው የሀገሪቱን ሰላም ለመመለስ ነው”ሲሉ ተደምጠዋል።
ሱዳን በዚህ የአፍሪካ ዋንጫ በአንድ ጨዋታ አሸንፋ እና በአንድ ጨዋታ ተሸንፋ ሦስት ነጥብ እና ሁለት የግብ ዕዳ በመያዝ በሦስተኛነት ተቀምጣለች።
ከሁለቱ ሀገራት አሸናፊ የሚኾነው ሀገር የሚያልፍ ይኾናል። በአንጻሩ ጨዋታው በአቻ ውጤት ከተጠናቀቀ ሱዳን ሁለት የግብ ዕዳ ስላለባት ጥሎ ማለፉን የምትቀላቀለው ቡርኪናፋሶ ትኾናለች።
ቡርኪናፋሶም በአንዱ አሸንፋ እና በአንዱ ተሸንፋ ሦስት ነጥብ በመያዝ በሁለተኛነት ትገኛለች። ሁለቱ ሀገራት ከ2012 ዓ.ም ወዲህ በአንድ ጨዋታ ተገናኝተው ሱዳን 2ለ1ማሸነፏ ይታዎሳል። ዛሬስ? የሚለው ደግሞ ተጠባቂ ነው።
በሌላ የምድብ አምስት ጨዋታ ኢኳቶሪያል ጊኒ ከአልጀሪያ እንዲሁም ሱዳን ከቡርኪናፋሶ በተመሳሳይ ምሽት 1:00 ላይ ይጫወታሉ።
ያደረገቻቸውን ሁለት ጨዋታዎች በመሸነፍ ያለ ምንም ነጥብ በደረጃው ግርጌ ላይ የተቀመጠችው ኢኳቶሪያል ጊኒ ምድቡን በስድስት ነጥብ እና በአራት የግብ ክፍያ እየመራች ከምትገኘው አልጀሪያ በስታዲ ልዑል ሙላይ አል ሐሰን ስታዲየም ትጫወታለች።
ሁለቱ ቡድኖች እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከ2022 ወዲህ በሦስት የካፍ ጨዋታዎች ተገናኝተው አንዳንድ ጊዜ ሲያሸንፉ በአንድ ጨዋታ አቻ ተለያይተዋል።
አልጀሪያ ማለፏን ያረጋገጠች ሲኾን የኢኳቶሪያል ጊኒ መሰናበትም እርግጥ ኾኗል። ዛሬ ሁለቱም ቡድኖች 4-3-3 አሰላለፍን ይተገብራሉ ነው የተባለው።
በምድብ ስድስት ከአፍሪካ ዋንጫ የተሰናበተችው ጋቦን ምድቡን በአራት ነጥብ ከምትመራው አይቮሪ ኮስት ምሽት 4:00 ላይ ትጫወታለች።
በተመሳሳይ ሰዓት በሦስት ነጥብ በሦስተኛነት የተቀመጠችው ሞዛምቢክ አራት ነጥብ ይዛ በሁለተኛነት ከምትገኘው ካሜሩን ጋር ይጫወታሉ።
በዚህ ምድብ ከጋቦን በስተቀር አሸናፊ የሚኾኑት ሀገራት በቀጥታ ጥሎ ማለፉን መቀላቀል ስለሚችሉ ጨዋታዎች ብርቱ ፉክክር ይደረግባቸዋል ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here