ደሴ ከተማ ዛሬ ወሳኝ ጨዋታን ያደርጋል።

0
34
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በሁለት ምድብ ተከፍሎ ጨዋታዎችን እያስተናገደ ይገኛል።
ዛሬ በዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር ምድብ “ለ” ላይ በጅማ ስታዲየም ቀን 7:00 ላይ መንጌ ቤላሻንጉል ከአዲሰ ከተማ ክፍለ ከተማ እንዲሁም ሀላባ ከተማ ከደሴ ከተማ 9:30 ላይ የሚጫወቱ ይኾናል።
የአማራ ክልል ተወካዩ ደሴ ከተማ እስካሁን ስምንት ጨዋታዎችን አድርጓል። 13 ነጥብ እና አምስት የግብ ክፍያ በመያዝም በደረጃ ሰንጠረዡ በሁለተኛነት ተቀምጧል።
ቅኝቶቹ ከምድቡ መሪ ሀላባ ከተማ ያላቸው የነጥብ ልዩነት አንድ የግብ ክፍያ እና ሦስት ነጥብ ነው።
ቡድኑ በሰባተኛ ሳምንት ከሶሎዶ ዓድዋ ጋር ዜሮ ለዜሮ በመለያየት በስምንተኛው ሳምንት መርሐ ግብር በጉዳት ምክንያት አጥቷቸው የነበሩ ተጨዋቾችን ማሰለፍ በመቻሉ አዲስ አበባ ከተማን 4ለ2 ማሸነፉ ይታወሳል።
ቡድኑ ከጨዋታ ጨዋታ እየተጠናከረ ስለመምጣቱ እየተመዘገቡ የሚገኙ ውጤቶች ተናጋሪዎች ናቸው።
ደሴ ከተማ የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ ደረጃውን ከምድቡ መሪ ጋር በነጥብ የሚያስተካክል ይኾናል።
ምድብ “ለ”ን ሀላባ ከተማ በአንደኛነት እየመራ ሲኾን ደሴ ከተማ በሁለተኛነት እና መንጌ ቤላሻንጉል በሦስተኛነት ተቀምጠዋል።
ደብረ ብርሃን ከተማ ደግሞ በአምስተኛነት ተቀምጧል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here