ሊቨርፑል የቆመ ኳስ አሠልጣኙን አሰናበተ።

0
33
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የመርሲሳይዱ ሊቨርፑል በዚህ የውድድር ዘመን 12 ግቦች ከቆመ ኳስ ተነስተው ተቆጥረውበታል። በአንጻሩ የቆመ ኳስን በመጠቀም ያስቆጠረው ግብ ብዛት ሦሥት ብቻ ነው።
ይህም የቆመ ኳስ አሠልጣኙ ድክመት ነው ብሎ የገመገመው ክለቡ አሠልጣኝ አሮን ብሪግስን ማሰናበቱን ቢቢስ ዘግቧል።
ሊቨርፑል በሊጉ ካደረጋቸው 18 ጨዋታዎች 10አሸንፎ፣ በሁለት አቻ ተለያይቶ እና በስድስት ተሸንፎ 32 ነጥብ በመያዝ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ዘጋቢ፦ ሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here